Skip to main content
King County logo

የምግብ ደሕንነት ምዘና ክፍፍሎች

ምግብ ቤቶች ስለ አመጋገብ የተረጋገጠ ውሳኔዎችን እንዲያደርጉ ለመርዳት፤ ስለ ምግብ ቤቶች የምግብ ደሕንነት ልምምዶች የበለጠ መረጃ ለማሕበረሰቡ ለማቅረብ፤ ከአራቱ የምግብ ደሕንነት ምዘናዎች አንዱን ያገኛሉ፡፡ አንድ ምግብ ቤት ለስራ ክፍት ከሆነ፤ ለመስራት ቢያንስ ፤ ዝቅተኛውን የምግብ ደሕንነት ደረጃዎች ያሟላል፡፡

 • ማሻሻል አለበት
  ባለፈው ዓመት ውስጥ ምግብ ቤቱ በሕዝብ ጤንነት- ሲያትል እና ኪንግ ካውንቲ ተዘግቶ ነበር ወይም ምግብ ቤቱ የምግብ ደሕንነት ልምምዶችን ለማስተካከል ተደጋጋሚ የመልሶ ምርመራ ማድረግ ይኖርበታል፡፡

 • ደሕና
  ምግብ ቤቱ፡ ባለፉት አራት ምርመራዎች ብዙ ቀይ አደገኛ ጥሰቶች ነበሩት፡፡


 • ጥሩ፡፡
  ምግብ ቤቱ፡ ባለፉት አራት ምርመራዎች አንዳንድ ቀይ አደገኛ ጥሰቶች ነበሩት፡፡


 • እጅግ በጣም ጥሩ
  ምግብ ቤቱ፡ ባለፉት አራት ምርመራዎች ምንም ወይም ጥቂት ቀይ አደገኛ ጥሰቶች ነበሩት፡፡

ከምግብ ቤቶች ምዘና በስተጀርባ ያለው ምንድን ነው?

የምግብ ቤቶች የምዘና ክፍፍል የሚወሰነው በሶስት ዋና ዋና አካላት ነው:

 • በጊዜያት ውስጥ ያሉ የምግብ ደሕንነት ልምምዶች ሂደት፡፡ጥሩ የምግብ ደሕንነት በየዕለቱ መተግበር አለበት፡፡ የምግብ ደሕነት ምዘና የመስኮት ምልክቶች ምግብ ቤቶች በአንድ ነጠላ ምርመራ ብቻ ሳይሆን፤ በረዥም ጊዜያት ውስጥ ምን ያሕል እየተንቀሳቀሱ እንዳለ ያሳያል፡፡ የምግብ ቤቶች የምግብ ደሕንነት ምዘና የሚወሰነው ከምግብ ቤቱ ያለፉት አራት ተከታታይ ምርመራዎች የቀይ አደገኛ ጥሰት ነጥቦች ነው፡፡

 • የብቃት ደረጃ፡፡የኪንግ ካውንቲ ነዋሪዎች፤ ምግብ ቤቶች ምርመራውን ማለፋቸውን ወይም መውደቃቸውን ባለፈ ማወቅ ይፈልጋሉ፡፡ የምግብ ቤት መስኮት ምልክቶች፤ ምግብ ቤቶች ዝቅተኛውን የመስፈርት ደረጃ ከማሟላት ባለፈ ምን ያህል የምግብ ደሕንነት ልምምዶችን እንደሚለማመዱ ያሳያል፡፡

 • በስፍራ ያለ ምዘና ፡፡የኪንግ ካውንቲ ነዋሪዎች በአቅራቢያቸው ካሉ ከሌላ ምግብ ቤቶች አኳያ ሲነፃፀር፤ ምግብ ቤቶች እንዴት የምግብ ደሕንነትን እንደሚለማመዱ ማወቅ ይፈልጋል፡፡ የእያንዳንዱ ምግብ ቤቶች አማካይ ውጤት በተመሳሳይ ዚፕ ኮድ ወይም መልከዓምድራዊ አካባቢ ካሉ ከሌሎች ምግብ ቤቶች ጋር ይፃፀራል፡፡

በእያንዳንዱ ክፍፍል ስር የሚመደቡ የምግብ ቤቶች አቅራቢያዊ የፐርሰንቴጅ ዝርዝር እንደሚከተለው ነው፡፡ በስፍራ ያለ ምዘና የሚተገበረው ‘እጅግ በጣም ጥሩ’፣ ‘ጥሩ’ እና ‘ደሕና’ ለሚባሉት ለከፍተኛ 3 ክፍፍሎች ነው ፡፡ ‘ማሻሻል ይገባቸዋል’ ተባሉት ክፍሎች በአካባቢ አይመዘኑም፡፡

ቀይ አደገኛ ጥሰት ምንድን ነው??

እነዚህ የምግብ አያያዝ ልምምዶች፤ እንደሚገባው ካልተተገበሩ፤ በእርግጠኝነት ወደ ምግብ ወለድ በሽታዎች ያመራሉ፡፡

Steps to safe food handling


የምግብ ደሕንነት ምዘና ስርዓት ድሕረገፅ