Skip to main content

በኪንግ ካውንቲ ክትባት ማግኘት

በኪንግ ካውንቲ ክትባት ማግኘት

ኤፕሪል 28, 2023 የተሻሻለው (ቢቫለንት) ክትባት እድሜያቸው 6 ወር እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ሰዎች ይመከራል።

ከኤፕሪል 19,2023 ጀምሮ የሲዲሲ COVID-19 ክትባት ምክሮች፡፡

ዕድሜው 6 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆነ ማንኛውም ሰው 1 የተሻሻለውን የፒፋይዘር ወይም የሞደርና COVID-19 ክትባት ከወሰደ (እንግሊዝኛ ብቻ) ወቅታዊ ክትባት እንደወሰድ ይቆጠራል።

አንዳንድ ሰዎች ተጨማሪ የኮቪድ፡ COVID-19 የማጠናከሪያ ዙር ክትባቶች ሊያገኙ ይችላሉ፡፡

  • እድሜያቸው 65 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎች 1 ተጨማሪ የትሻሻለ COVID-19 4ኛ ማጠናከሪያ ዙር ክትባት ወይንም መጀመሪያ ከተሻሻለው COVID-19 ክትባት ከውሰዱ ተጨማሪ ወራት በኋላ ሊያገኙ ይችላሉ።
  • መካከለኛ ወይም ከባድ የበሽታ መከላከያ ችግር ያለባቸው ሰዎች 1 ተጨማሪ የተሻሻለውን COVID-19 2ኛ ማጠናከሪያ ዙር ወይንም መጀመሪያ ከተሻሻለው COVID-19 ክትባት ከውሰዱ ተጨማሪ ወራት በኋላ ሊያገኙ ይችላሉ።

እድሜያቸው ከ6 ወር እስከ 5ዓመት የሆኑ ህጻናት ብዙ COVID-19 ክትባት ሊፈልጉ ይችላሉ፣ ቢያንስ 1 የተሻሻለ የፒፋይዘር ወይም ሞደርና ክትባት። ቀደም ሲል በተቀበሉት የክትባት መጠን እና በእድሜ ላይ የተመሰረተ ነው።

ምን ያህል መጠን እንደሚፈልጉ ጥያቄዎች ካለዎት እባክዎን የጤና እንክብካቤ አቅራቢዎን ያነጋግሩ።


ክትባቱን እንዴት ማግኝት እንደሚቻል ያሉ መረጃዎች በተደጋጋሚ ይሻሻላሉ። እነዚህ ማሻሻያዎች በፍጥነት እንዲተረጎሙ እየሰራን ቢሆንም፣ ትርጉሙን ለመስራት እና ድህረ-ገጽ ላይ ለመለጠፍ በሚወሰደው ጊዜ ምክኒያት መጓተት ሊኖር ይችላል። ለትእግስትዎ እናመሰግናለን።

በእንግሊዘኛ ያሉ በጣም በቅርብ ጊዜ የተሻሻሉ መረጃዎችን ከ kingcounty.gov/vaccine (ድህረ-ገጹ በእንግሊዘኛ ብቻ ነው ያለው) ማግኘት ይችላሉ።

እንዴት መከተብ ይቻላል

ክትባቱ ለማንኛውም ሰው ነጻ ነው. ኢንሹራንስ ቢኖሮትም ባይኖሮትም፣ ዜግነት ቢኖሮትም ባይኖሮትም ፣ ወይም የኢሚግሬሽን ሁኔታዎት ምንም ይሁን ምን ክትባቱን በነጻ ያገኛሉ።

ምንም እንኳን የሞደርናን ወይም የፋይዘርን የመጀመሪያውን ዙር ክትባት ሌላ ቦታ ቢወስዱም ሁለተኛውን ዙር ክትባት በአብዛኛዎቹ ጣቢያዎች ላይ መውሰድ ይችላሉ ፡፡ እባክዎን የክትባት ካርዶትን ወይም የመጀመሪያዎን ክትባት ዙር የወሰዱበትን ካርድ ፎቶምስል ይዘው ይምጡ።

በራሪ (PDF):

Drive through vaccination site

እነዚህን ማምጣት ይገባዎታል፡

  • የልደት ቀን ያለው መታወቂያ፡የሠራተኛ መታወቂያ ወይም በግዛት፣ በጎሳ ወይም በፌዴራል-የተሰጠ መታወቂያ። ስምዎትን እና አድራሻዎትን የያዘ የክፍያ ወረቀት ወይም የባንክ ደብዳቤም መጠቀም ይችላሉ።
  • በላይኛው ክንድዎ ውስጥ መከተብ እንዲችሉ በቀላሉ ለመጠቅለል ቀላል የሆኑ አጭር እጀታዎችን ወይም የተለቀቁ እጀታዎችን ይልበሱ።
  • ስልጣን ባለው አዋቂ ሰው የተሰጠ ፈቃድ: ዕድሜዎ ከ18 ዓመት በታች ከሆነ: ክትባት ለማግኘት ስልጣን ካለው አዋቂ ሰው ፈቃድ ማግኘት ያስፈልግዎታል። ከቤተሰብ ነጻ ሆነው የሚኖሩ ከሆነ : አዋቂ ሰው አግብተው ከሆነ: ወይም የክትባት ጣቢያው የበሰሉ/አዋቂ ልጅ (mature minor) መሆንዎትን ከወሰነ ለራስዎ ፈቃድ መስጠት ይችላሉ። ሁሉም የክትባት ጣቢያዎች የበሰለ/አዋቂ ልጅ ውሳኔዎችን ሊሰጡ አይችሉም። ልጆችንና ወጣቶችን እንዲሁም ስልጣን ያለው አዋቂ ሰው ጨምሮ ትርጉማቸው ምን ማለት እንደሆነ ከዚህ በታች ተካቷል። ስልጣን ያለው አዋቂ ሰው በክትባት ቀጠሮው ላይ ከርስዎ ጋር የማይገኝ ከሆነ ስልጣን ያለውን አዋቂ ሰው ማረጋገጫ ወይም በህግ ነጻ መሆንዎትን የሚያረጋግጡ ማስረጃዎችን ለማሳየት የሚያስፈልጉ ነገሮችን በተመለከተ ክትባቱን ከሚስጥዎት ድርጅት ያጣሩ።
  • የእርስዎ ሲዲሲ የክትባት ካርድ: የሲዲሲ ክትባት ካርድዎ ሁለተኛ ዙር ወይም የማበረታቻ ክትባቶች የሚዎስዱ ከሆነ አዲስ የወሰዱት መጠን ወደ ካርዱ ይመዘገባል።

እንዴት መድረስ እንደሚቻል

የሚኖሩበት ቦታ ኪንግ ካውንቲ ከሆነና ወደ ክትባት ቦታ ለመድረስ ማጓጓዣ የሚያስፈልግዎ ከሆነ ብዙ ኣማራጮች ኣሉ።

  • የመጓጓዣዎች አገልግሎት፥ ወደ ክትባት ቀጠሮዎ ለመሄድ የመጓጓዣ አገልግሎት ከፈለጉ ፣ www.findaride.org ን ይጎብኙ ወይም ወደ ትራንስፖርት መርጃዎች መስመር በ425-943-6760 ይደውሉ (ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 8:30 a.m እስከ ምሽቱ 4 p.m። ለትርጉም 5 ይደውሉ)። አስተርጓሚ ከፈለጉ የሚፈልጉትን ቋንቋ ይናገሩ።
  • የአውቶቡስ አገልግሎቶች፥ የኪንግ ካውንቲ ሜትሮ ብዙ የመጓጓዣ አማራጮችን ለክትባት ቀጠሮዎች ያቀርባል፣ የአውቶቡስ ትራንዚትን ጨምሮ፣ የጋራ መጓጓዣን እና የኮሚኒቲ ቫን ማመላለሻዎችን ጨምሮ። ከኪንግ ካውንቲ ሜትሮ ስለ ትራንዚት አማራጮች የበለጠ ይረዱ፡፡ ወይም 206-553-3000 ይደውሉ።
  • የሜዲኬድ ወይም ኣፕል ሄልዝ ካርድ ካለዎት ሆፕ ሊንክ ሜዲኬድ 800-923-7433 በመደወል (ብቁነትዎን ያረጋግጡ)
  • በዕድሜ የገፉ ወይም የኣካል ጉዳተኛ ከሆኑ ሜትሮ ኣክሰስ 206-205-5000 ይደውሉ። (ብቁነትዎን ያረጋግጡ)
  • ለበርካታ ሰዎች መጓጓዣ ለማመቻቸት እየጣሩ ነው? ይህንን ቅጽ ይሙሉ ና የሆፕሊንክ ሞቢሊቲ (Hopelink Mobility Management team) ኣባል ሁኔታውን ለመከታተል ከርስዎ ይገናኛል።

ለሁለተኛው የማጠናከሪያ ክትባት ቀጠሮ ይያዙ

የመጀመሪያውን የማጠናከሪያ ክትባት/ዶዝ ከወሰዱ በኋላ በክትባት ቀጠሮዎ ቦታ ለሁለተኛው የማጠናከሪያ ክትባት /ዶዝ ቀጠሮ ይያዙ። ሁለተኛውን የማጠናከሪያ ክትባት /ዶዝ መውሰድ ያለባችሁ (ለፋይዘር/ Pfizer እና ኖቫቫክስ/Novavax) የመጀመሪያውን ማጠናከሪያ ከወሰዳችሁ ከ21 ቀናት በኋላ ወይም (ለ ሞደርና/Moderna) ከ 28 ቀናት በኋላ ነው።

በሽታ የመከላከል ስርዓትዎ በተሻለ ሁኔታ እንዲከላከልልዎ ሁለት የማጠናከሪያ ክትባት /ዶዝ መውሰድዎ ተከታታይ የመጀመሪያ ዙር ክትባትዎ እንዲጠናቀቅ ያደርጋል።

እባክዎን ያስተውሉ፦ በሽታ የመከላከል አቅማቸው የተዳከመ ሰዎች የተለያዩ የCOVID-19 የመጀመሪያ ደረጃ ክትባቶች እንዲወስዱ ይመከራሉ።

የማጠናከሪያ ክትባት/ዶዝ ቀጠሮ ይያዙ

ማጠናከሪያ ክትባቶቸ የመከላከል ጥንካሬን እና ዘመንን ለመጨመር የሚሰጡ ተጨማሪ የክትባት መርፌዎች ናቸው። በተለይ ከ50 አመት በላይ ለሆኑ አዋቂዎች እና የጤና ችግር ያለባቸው ሰዎች ማጠናከሪያ ክትባቶቸ ማግኘታቸው በጣም አስፈላጊ ነው።

የማጠናከሪያ ክትባት/ዶዝ ማን እንደሚያገኝ፣ መቼ እንደሚወሰድ እና የትኛውን አይነት ማግኘት እንዳለበት ወቅታዊ መመሪያ፡

የመጀመሪያዎቹ ተከታታይ የመከላከያ ክትባቶች ዓቅም በጊዜ ሂደት መዳከም ሲጀምሩ በሽታ የመከላከል አቅምን ለማሳደግ ሁሉም ሰው የማጠናከሪያ ክትባት ቡስተር መውሰድ አለበት።

የማጠናከሪያ ዙር ክትባት ማን ማግኘት እንደሚችል፣ መቼ እንደሚወሰዱት እና የትኛውን አይነት ማግኘት እንዳለቦት ወቅታዊ መመሪያ:


በፌዴራል የሲቪል መብት ህግ መሰረት: የማህበረሰብ ጤና-ሲያትል እና ኪንግ ካውንቲ በማናቸውም ፕሮግራም ወይም ስራዎች ላይ ጥበቃ በሚደረግላቸው ግለሰቦች ምድብ: ሁሉንም ያካተተና በዘር ሳይገደብ : በመልክ: በመጡበት የትውልድ ስፍራ/አገር: ሃይማኖት: የጾታ ማንነት (የጾታ አገላለጽን አካቶ):የጾታ ኦሪየንቴሽን: የአካል ጉዳተኛነትን: እድሜ: እና የጋብቻ ሁኔታ ላይ መሰረት ያደረገ ማናቸውንም ልዩነቶች አያደርግም። ቅሬታ ካልዎትና ክስ መመስረት ከፈለጉ: ወይም አድሎአዊነትን በተመለከተ ጥያቄ ካልዎት እባክዎትን የኪንግ ካውንቲ የሲቪል መብቶች ፕሮግራምን በ civil-rights.OCR@kingcounty.gov206-263-2446(እባክዎትን ለትርጉም አገልግሎት ቋንቋዎትን ይግለጹ); TTY ሪሌይ 7-1-1; ወይም በፖስታ አድራሻ (401 5th Ave, Suite 800, Seattle, WA 98104) ያግኙ።


Link/share our site at kingcounty.gov/vaccine/amharic

expand_less