Skip to main content

COVID-19ን ለማስቆም የህዝብ ጤና ምክሮች (Amharic)

COVID-19ን ለማስቆም የህዝብ ጤና ምክሮች

Public Health Recommendations to Stop COVID-19 in Amharic

ኤፕሪል 28, 2023 የተሻሻለው (ቢቫለንት) ክትባት እድሜያቸው 6 ወር እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ሰዎች ይመከራል።

ከኤፕሪል 19,2023 ጀምሮ የሲዲሲ COVID-19 ክትባት ምክሮች፡፡

ዕድሜው 6 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆነ ማንኛውም ሰው 1 የተሻሻለውን የፒፋይዘር ወይም የሞደርና COVID-19 ክትባት ከወሰደ (እንግሊዝኛ ብቻ) ወቅታዊ ክትባት እንደወሰድ ይቆጠራል።

አንዳንድ ሰዎች ተጨማሪ የኮቪድ፡ COVID-19 የማጠናከሪያ ዙር ክትባቶች ሊያገኙ ይችላሉ፡፡

  • እድሜያቸው 65 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎች 1 ተጨማሪ የትሻሻለ COVID-19 4ኛ ማጠናከሪያ ዙር ክትባት ወይንም መጀመሪያ ከተሻሻለው COVID-19 ክትባት ከውሰዱ ተጨማሪ ወራት በኋላ ሊያገኙ ይችላሉ።
  • መካከለኛ ወይም ከባድ የበሽታ መከላከያ ችግር ያለባቸው ሰዎች 1 ተጨማሪ የተሻሻለውን COVID-19 2ኛ ማጠናከሪያ ዙር ወይንም መጀመሪያ ከተሻሻለው COVID-19 ክትባት ከውሰዱ ተጨማሪ ወራት በኋላ ሊያገኙ ይችላሉ።

እድሜያቸው ከ6 ወር እስከ 5ዓመት የሆኑ ህጻናት ብዙ COVID-19 ክትባት ሊፈልጉ ይችላሉ፣ ቢያንስ 1 የተሻሻለ የፒፋይዘር ወይም ሞደርና ክትባት። ቀደም ሲል በተቀበሉት የክትባት መጠን እና በእድሜ ላይ የተመሰረተ ነው።

ምን ያህል መጠን እንደሚፈልጉ ጥያቄዎች ካለዎት እባክዎን የጤና እንክብካቤ አቅራቢዎን ያነጋግሩ።

የክትባት ቦታዎችን እና ቀጠሮዎችን ለማግኘት በኪንግ ካውንቲ ውስጥ እንዴት ክትባት ማግኘት እንደሚቻል የሚገልጸውን ድህረገፅ ይጎብኙ።

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር እና የእርስ በርስ ደህንነትን ለመጠበቅ እንዲረዳ፤ እነዚህን እርምጃዎች ይውሰዱ።

ከሁሉ የተሻለው መከላከያ ክትባት መውሰድ ነው ሙሉ በሙሉ የተከተቡ ሰዎች አሁን ተጨማሪ ነገሮችን ደህንነታቸውን ጠብቀው ማከናወን ይችላሉ እንዲሁም በህብረተሰቡ ውስጥ የCOVID-19 ስርጭት እንዲቀንስ ያግዛሉ።

ከፍተኛ ተጋላጭነት በሚፈጠርባቸው ቦታዎች (ለምሳሌ በተጨናነቁ ቦታዎች) የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ ሁሉንም ሰው ለመጠበቅ ይረዳል። በተለይም ከክትባቱ ሙሉ ጥበቃ ሊያገኙ የማይችሉትን እንደ ህፃናት ልጆች እና ቫይረሱን ለመቋቋም የማይችሉ የጤና እክል ያለባቸውን ሰዎች ከበሽታው መጠበቅ በጣም አስፈላጊ ነው።

የ COVID-19 ምልክቶች ካለብዎ ወይም አዎንታዊ የምርመራ ውጤት ካለው ሰው ጋር በቅርብ የተገናኙ ከሆነ ይመርመሩ

COVID-19 ከተገኘብዎት ወይም ለበሽታው ከፍተኛ ተጋላጭ ከሆኑ የCOVID-19 ህክምና አስቀድሞ ማግኘት ከጠና ህመም እና ሆስፒታል ከመግባት ሊታደግ ይችላል። ህክምና የሚያስፈልግዎ መሆኑን ለማወቅ የጤና እንክብካቤ አቅራቢዎን ያማክሩ።

ያልተከተቡ ሰዎች የሚሳተፉ ከሆነ የተሳታፊዎችን ቁጥር ቀንሰው ዝግጅትዎን ከቤት ውጭ ያድርጉ። ቫይረሱ በቀላሉ በቤት ውስጥ ስለሚሰራጭ የንግድ ድርጅቶች እና መስሪያ ቤቶች በቤት ውስጥ ጥሩ የአየር ዝውውር እንዲኖር በማድረግ እና የአየር ማጣሪያዎችን (በቤት ውስጥ ጥሩ የአየር ፍሰት እና የአየር ማጣሪያዎችን በመጠቀም) (የእንግሊዝኛ ድረ-ገጽ) በመጠቀም ቫይረሱን በአየር ላይ መቀነስ ይችላሉ።

Caring for yourself or others

ለ COVID-19 ጋር እራስዎን ወይም ሌሎችን እንዴት እንደሚንከባከቡ

ቨድዮ ኢንፎግራፊክ

መመርመር ለመታከም /Test to Treat/ ሰዎች ተመርምረው COVID-19 ከተገኘባቸው በአፋጣኝ የነፃ ህክምና እንዲያገኙ የሚረዳ አዲስ ፕሮግራም ነው።

የበለጠ ለማወቅ



እርዳታ አለን

ለሌሎች ቋንቋዎች የትርጓሜ አገልግሎት ከፈለጉ ወይም በመስመር ላይ እገዛ ከፈለጉ፣ ወደ ዋሽንግተን ግዛት የ የመረጃ መስመር ይደውሉ። ስለ እርስዎ የኢሚግሬሽን ሁኔታ አንጠይቅም። ሁሉም ግለሰብ ያለበት ሁኔታ ምንም ይሁን ምን እርዳታ ማግኘት ይችላል።

አስተርጓሚ ለማግኘት:

  1. 1-800-525-0127
  2. መልእክት ይሰማሉ። የጥሪ ማእከል ኦፕሬተሩ መልስ እስኪሰጦት ድረስ ይጠብቁ።
  3. የሚፈልጉትን ቋንቋ ይናገሩ።
  4. የጥሪ ማእከል ኦፕሬተሩ የአስተርጓሚ አገልግሎትን ያቀርብሎታል። ይህ በሚሆንበት ጊዜ ስልኩን አይዝጉ። ከአስተርጓሚ ጋር እስኪገናኙ ድረስ ስልኩ ላይ ይቆዩ።

የ COVID-19 መምራዎች


ኢንፎግራፊክ


ቨድዮ

ለ COVID-19 ጋር እራስዎን ወይም ሌሎችን እንዴት እንደሚንከባከቡ

ለምንድነው ጨቅላ ህጻናት እና ህጻናት የኮቪድ ክትባት መውሰድ ያለባቸው?

ለታዳጊ ልጅዎ የኮቪድ ክትባት እንዴት እንደሚዘጋጁ

የማጠናከሪያ ዙር ክትባት መውሰድ ለምን አስፈለገኝ?

ትንሹ ልጃችሁ የኮቪድ ክትባቱን ሲወስድ ምን እንደሚጠበቅ


ፖስተሮች

የ COVID-19 አደጋ ለመቀነስ ሠራተኞቹ ምልክቶቹን በማተምና በመለጠፍ ከ ደንበኛ ጋር በመግባባት ይተባበራሉ።

እርስበርስ ለመረዳዳት ዝግጁ ሁኑ። ጠንካራ የመተሳሰብ ስሜት ከዚህ ከባድ ወቅት እንድናልፍ ይረዳናል።


Link/share our site at kingcounty.gov/covid/amharic

expand_less