Skip to main content

2021-2022 ኪንግ ካውንቲ ባጀት በአጭሩ

2021-2022 ኪንግ ካውንቲ ባጀት በአጭሩ

ኪንግ ካውንቲ ሚሊዮን ለሚሆኑ ሰዎች ወደ $12.4 ቢሊዮን የሚሆን የሁለት ዓመት በጀትን፣ ለ 15,000 ሠራተኞች እና ከ60 በላይ ለሚሆኑ የተለያዩ አገልግሎቶችን በጥልቀት ካጤነ በኋላ በአከባቢ እና በክልል አገልግሎቶችን ይሰጣል።

ማጠቃለያ

ኪንግ ካውንቲ በ2021-2022 ያልተለመደ የበጀት እጥረት እያጋጠመው ይገኛል። ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ የተነሳ የተከሰተው የኢኮኖሚ ውድቀት በሽያጭ ታክሲ ገቢዎች ላይ ቀጥተኛ የሆነ መቀነስ፣ በበርካታ የገንዘብ ምጮች ላይ ትርጉም ያለው ክፍተቶችን ወደ መፍጠር፣ ማለትም የምድር ባቡር የማጓጓዣ ዘዴን፣ አጠቃላይ የገንዘብ ገቢን፣ እና የአእምሮ ህመም እና የአደንዛዥ ዕጽ ተጽእኖ ሥር ላሉት የሚወጣ ገንዘብን አካቶ ቀጥተኛ ወደ ሆነ ቅነሳ አምርቷል።

ለ 2021-2022 የተንደፈው ባጀት ለነዋሪዎች አስፈላጊ የሆኑ አገልግሎቶችን በማስቀጠል፣ በጣም አስፈላጊ የሆኑ ፍላጎቶችን ማለትም ከባቢያዊ የሆኑትን ነገሮች በማሻሻል በመቀጠል፣ እና የካውንቲ የጸረ-ዘረኝነት አጀንዳን፣ ማለት የታሰበበትን እና ትርጉም ያለው የማኅበረሰብ ተሳትፎ ማድረግን አካቶ በማስጠበቅ በጀቱን ሚዛኑን የጠበቀ እንዲሆን ትኩረት ያደረጋል። ይህም በሚከተለው መንገድ ይሳካል፡

  • በአጠቃላይ የገንዘብ ኤጄንሲዎች እና የውስጣዊ አገልግሎቶች የወጪ እና የአገልግሎት ቅነሳዎች።
  • ጠንቅቆ አሳቢው ካውንቲው ባለፉት አስርቴ ዓመታት የገነባውን ተቀማጮችን ይጠቀማል።
  • አዲስ ገቢ፣ በኪንግ ካውንቲ ውስጥ በሕግ ያልተቋቋመ በጥቅም ሰጪዎች የመጠቀም መብት ባላቸው በትክክለኛ መንገድ በመጠቀም የሚከፈል የኪራይ ክፍያዎችን ያካትታል።
  • ወጀለኛ በሆነ የሕግ ሥርዓት ውስጥ ያለ አዲስ ሂደት ውስጥ ማዋዕለ ንዋይን ማፍሰስ በወደ ፊቱ ላይ መዋዕለ ንዋይ እንዳይፈስ የሚያደርግ ነው።
  • ውጤታማ የሆነ የሰው ሀብት አስተዳደር፣ በተቻለ መጠን ከሥራ መባረርን ለመቀነስ፣ የበጎ ፈቃደኞችን መለያ መርኃግብርን ያካትታል።

200917_10279w_KC_revenue_amh

200917_10279w_KC_expend_amh

200917_10279w_KC_taxable_sales_amh

የበጀት ማጠቃለያዎች

በ 2021-2022 የቀረበው የባጀት ረቂቅ የዘረኝነት ቀውስን መፍትሔ ለመስጠት ለመጀመር መዋዕለ ንዋይን ማስፍሰስን ያካትታል፤ ይህም የሚያጠቃልለው:

  • የወነጀለኛ የሕግ ሥርዓትን ማደስ።
  • አማራጭ የሆኑ የሕዝባዊ ደኅንነት መጠብቂያ ሞደሎችን በመፍጠር እና ተግባራዊ በማድረግ።
  • ከማኅበረሰብ ጋር በመሆን የአብሮነት መፍትሔዎችን መፍጠር።
  • ማኅበረሰብን-መሰረት ላደረጉት ድርጅቶች ዘላቂ የሆነ ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ማድረግን።
  • ጥቁር፣ የአገሩን ተወላጆች፣ እና ባለቀለም የሆኑ ሠራተኞ ሕዝቦችን መርዳት።

እነዚህ ጥረቶች በርካታ የሆኑ የበጀት ዕደቶችን - ከታችኛው ምንጭ ወደ ላይኛው ምንጭ ምላሽ የመስጠት መርኃግብን ማለትም የካውንቲን ትኩረት ከወነጀለኝነት ፍትሕ ወደ አንዱ የዘር እና የማኅበረሰብ ፍትህ ሥርዓት ለመለወጥ የሚቀጥለውን የረጅም ጊዜ ስልት አካል ናቸው።

የአየር ለውጥ አንዱ የአከባቢያው እና ለትውልዳችን የምጣኔ ሀብት ተግዳሮት መለኪያ ነው። በ 2021-2022 የቀረበው የባጀት ረቂቅ የአከባቢ ተፈጥሮአችንን የሚጠብቅ እና የሚያድስ ተግባራትን ይወስዳል፤ ነዋሪዎች እና ሥራዎች እንዲላመዱ ይረዳል፤ ደግሞም እኩልነት ያለው ንጽሑህ ወደ ሆነው የኃይል ምጣኔ ሀብት ይመራል። የኪንግ ካውንቲ አከባቢ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ነገሮች የሚያካትቱት፡

  • ጤናማ የሆነ የውኃ ጥራት እና ነዋሪዎች እንዲኖሩ ማድረግ።
  • አረንጓዴ ቦታዎች ማቆየት፣ መፍጠር እና እኩልነት ያለበትን በማድረግ እና የተፈጥሮ ሥርዓቶች ቶሎ እንዲያገግሙ ማድረግ።
  • በታሪክ ለተጠቁ ማኅበረሰቦች የሥራ ዕድልን የሚፈጥሩ መንገዶችን ንጹህ የሆነ የኃይል ምጣኔ ሀብት መፍጠር እና የአከባቢያችን ግንባታ ለአየር ጠባዩ ወደፊት ተስማም የሆነውን ማስተላለፊ ነው።
  • የሚጣሉ ቆሻሻዎችን በማስተዳድር ረገድ የሚጣሉ ቆሻሻ ሀብቶችን ወደ ዜሮ ለማምጣት የተሃድሶውን በማፋጠን።

በምድር ባቡር መጓጓዣ ውስጥ የመሬቱ አቀማመጥ ሥራዎች ኮቪድ ወረርሽኝ በገቢ እና ጋላቢነት ላይ ትርጉም ባለው መልኩ ወደ መቀነስ ባመራበት ጊዜ በሚገርም ሁኔታ ተለውጧል። የምድር ባቡር የ 2021-2022 የቀረበው የባጀት ረቂቅ የእንቅስቃሴ ሥርዓቶችን መልሶ በማደስ እና መልሶ በመገንባት ላይ ትኩረት ያደርጋል፤ የሚያደርግባቸውም፡

  • በኮቪድ -19 ወረርሽኝ ወቅት አስፈላጊ ለሆኑ ሠራተኞች ከቦታ ቦታ እንቅስቃሴ እና የመሸጋገሪያን ላይ መሰረት ያደረጉ ተጓዦችን ዕድል እንዲያገኙ ማስቻል እና ተጓዦች ወደ መሸጋገሪያ መመለስ በሚጀምሩበት ጊዜ የማገገሚያ ስልትን ተፈጻሚ ማድረግ።
  • ከመርከብ የሚለቀቁትን ልቀቶችን ወደ ዜሮ ማድረግ የሚለው ላይ 100 ፐርሰንት መዋዕለ ንዋይ ማፍሰሱን መቀጠል።
  • አዳዲስ የሆኑ ግብረገብነት ያላቸውን ማስገደጃዎች እና መምሪያዎችን ሞዴሎችን እንዲመለከቱ ከማኅበረሰብ ጋር መስራት።
  • ዓመታዊ የማለፍ መርኃግብን ላይ የሚደረገውን ቅናሽን ማዘጋጀት።
  • የግብረገብ ሥራዎችን መጨመር እና በነጂዎች እና በነጂነት ላይ ያላቸውን ተጽእኖ እስከ 2023 ድረስ ማዘግየት።
  • ከቦታ ቦታ እንቅስቃሴ ጋር ባለው ማዕቀፍ ጋር ወጥነት ያላቸውን መምሪያዎችን ማዘመን።

ከኮቪድ-19 የቤት አልባ የሆኑ ሰዎች ምላሽ የተገኘውን ትምህርት በትምህርቶቹ ውስጥ በመገንባት፣ የ 2021-2022 ረቂቅ በጀት ቤት አልባ የሆኑ ሰዎችን ችግር ለመቅረፍ ተጨባጭ የሆነ እርምጃ በሚከተለው መንገድ ይወስዳል፡

  • ቤት አልባ በሆኑ ሰዎች ላይ የአጭር ጊዜ እና የረጅም ጊዜ ትርጉም ያላቸው በጎ ተጽእኖዎችን በማድረግ።
  • ቤት የሚያገኙበትን ዕድል በመጨመር።
  • ዋጋቸው ተመጣጣኝ የሆኑ ቤቶችን ልማት በማፋጠን።
  • በአዲሱ የኪንግ ካውንቲ የክላላዊ የቤት አልባ ሰዎች ባለሥልጣን ውስጥ አፈጻፈምን በመቀጠል የቤት አልባ ሰዎችን የቀውስ ምላሽ ላይ ክላልዊውን ትብብር በማሻሻል።

የሥነልቦና ጤና አገልግሎቶች፣ በተለይም ደግሞ ኮቪድ-19 ባሳደረው ተጽእኖዎች ላይ የተሰጠው የጤና እና የሥነልቦና አገልግሎት በከፍተኛ ደረጃ የሚፈለጉ ናቸው። በተመሳሳይ ሁኔታ፣ ኪንግ ካውንቲ ከግዛቱ ገቢዎች መጣበብ የተነሳ እና ከወጪዎች መጨመር የተነሳ፣ በተለይም ደግሞ በተለይም ደግሞ እነዚያ ያለውዴታ ህክምና የማግኘት አዋጅ ፍርድ ቤት ጋር ከተያያዙት የተነሳ ለሥነ ልቦና የጤና አገልግሎቶች የገንዘብ ማጣት ቀውስ እየገጠመው ይገኛል። በ 2021-2022፣ ኪንግ ካውንቲ አብዛኛውን ለህክምና ያልሆነ ደንበኞችን ለማቋቋም ከአሁን በኋላ ገንዘብ መስጠት የማይችል ሲሆን በርካታ የሆኑ ውድ የሆኑ ቀውስ የሚያመጡ ሥርዓትችን ተጽእኗቸውን ይቀንሳል። ሌሎች የገንዘብ ምጮች መቅረት ወይም የመንግሥት ሕጋዊ እርምጃዎች፣ ለመድኃኒት እርዳታ ያልሆኑ ገንዘብ የሚወጣባቸውን መርኃግብሮችን በጥልቀት ማቋረጡ ከ2022 ጀምሮ አስፈላጊ ይሆናል። የማያቋርጥ ሥልጣን ይህን ክፍተት ለመሸፈን አዲስ የገቢ ምንጭ ሀሳብ እያቀረበ ሲሆን በቋሚነት የመኖሪያ ቤት ድጋፍን ይሰጣል፤ ይህም ማለት በዚያ በሚኖሩ ግለሰቦች የሚፈለጉትን አገልግሎቶች ጋር የመኖሪያ ቤትንም ያጣምራል።

አገልግሎቶችን እና ሥራዎችን በሚያቆዩበት ጊዜ ወጪዎችን ለመቀነስ የሚደረገው ጥረት፣ የማያቋርጥ ባለሥልጣን በ2021-2022 የበጀት ዓመት ውስጥ የመካከለኛ ከተማ የቢሮ ቦታን ለማጠናከር፣ የአስተዳደር ሕንጻን መዝጋት እና ደንበኞችን ፊት ለፊት የሚያገኛቸውን አገልግሎቶችን ቁጥር በ King Street Center ላይ በአንድ ላይ ማስቀመጥን አካቶ ሀሳብ እያቀረበ ይገኛል።

የኪንግ ካውንቲ የእግር አሻራን በጥቅት ሕንጻዎች ላይ ማጠናከር፡

  • መጠቀሚያዎችን፣ የሕንጻ ጥገናን፣ እና የቦታ ወጪዎችን ይቀንሳል።
  • ነዋሪዎችም የካውንቲ አገልግሎቶችን ለማግኘት ቀላል ያደርግላቸዋል።
  • የካውንቲውን የካርቦን አሻራን ይቀንሳል።
  • ከወረርሽኙ በኋላ በርቀት ሥራ ለመቀጠል ብዙ ሠራተኞች ያላቸውን ፍላጎታቸውን የሚደግፍላቸው ይሆናል።

ኪንግ ካውንቲ በሕግ ባልተቋቋመ ቦታዎች ላይ በግርድፉ ወደ 250,000 ሰዎች የአከባቢው የአግልግሎት አቅራቢ ነው። የአከባቢው የአገልግሎቶች የመምሪያ ክፍል፣ ከሌሎች የካውንቲ ኤጄንሲዎች ጋር በመሆን፣ በካውንቲው የሚሰጡትን አገልግሎቶች፣ መርኃግብሮች፣ እና መሰረተ ልማቶችን ለማሻሻል የማኅበረሰብን ተሳትፎ እና ውሳኔ ሰጪነትን በማስፋት በየሁለት ዓመቱ የሚደረገውን የበጀት ሂደት ውስጥ የማኅበረሰብ-መር ግብዓትን ቅድሚያ እየሰጠው ይገኛል።

ቁልፍ የሆነ የ 2021-2022 የመዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ ረቂቅ ዕቅድ የሚያጠቃልለው፡

  • ከማሪዋና ችርቻሮ ሽያጭ የሚገኘውን የግብር ገቢን መሽጫዎቹ በሚገኙባቸው ያሉትን ማኅበረሰብ ላይ መልሶ መዋላቸውን ለማረጋገጥ ከማሪዋና የችርቻሮ ሽያጭ ግብር የሚገኘውን ገንዘብ የ Sheriff በጀትን ወደ ሌላ አቅጣጫ መውሰድ።
  • ተሳታፊ በሆነ የባጀት ሂደት በኩል፣ ማለትም በ Skyway ማዕከል ውስት ለማኅበረሰብ አማራጮችን መፈለግን አካቶ የማኅበረሰቡን ፍላጎቶችን ለመደገፍ ሁለት አዳዲስ የገንዘብ ፕሮጄክቶችን መቅረጽ።
  • የሕንጻውን ውጤታማነትን ለማሻሻል፣ የውኃ አጠቃቀሙን ለመቀነስ እና የሚባክነው የግንባታ ብክነትን ለመቀነስ ለ Green ሕንጻ መርኃግብሮችን ለመርዳት ያለው የገንዘብ ድጋፍ ይቀጥላል።
  • ከ$20 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለክፍት ቦታ ለማቆየት የሚውል ይሆናል።

ከሕዝባዊ ጤና በፊት እንኳን - ስያትል እና ኪንግ ካውንቲ በጃንዋሪ 2020 ላይ ለኮቪድ-19 መፈንዳት ምላሽ ለመስጠት የአደጋ ጊዜ ድርጊት ማዕከል አቋቁሟል፤ ኪንግ ካውንቲ ለወረርሽኙ እየተዘጋጀ ነበር። በቀጣዩ ወራት፣ ኪንግ ካውንቲ በሽታውን ለመዋጋት ለክልላዊ ምላሽ ሰዎችን ለማንቀሳቀስ የሚተኩ ተግባራዊ እርምጃዎችን ወስዷል። ሆኖም ግን፣ ከተጨማሪ የፌድራል ወይም የግዛቱ የገንዘብ ድጋፍ ውጪ፣ አብዛኛዎቹ እነዚህ መርኃግብሮች በ 2021 ጅማሮ ላይ ይጠናቀቃሉ።

የታሰበበት እና ትርጉም ያለው የማኅበረሰብ ተሳትፎ እና አብሮ ፈጣሪነት ለኪንግ ካውንቲ ለእኩልነት ድጋፍ፣ ወደ የዘር ፍትሐውነት የሚመራውን እሴትን መኖር፣ እና ዘረኝነትን እንደ ሕዝባዊ የጤና ቀውስ አድርጎ በውጤታማነት መፍትሔ በመስጠት ላይ ላለው ስኬት መስረቱ ነው። ለ 2021-2022 የቀረበው የባጀት ረቂቅ የካውንቲንው አካሄድ ወደ አብሮ ፈጣሪነት፣ እና የረጅም ጊዜ ስኬታማ የሆነ የማኀበረሰብ መሰረት ያላቸውን ድርጅቶችንድ በመርዳት ለውጥ ለማምጣት መዋዕለ ንዋይ ፈሰስ ያደርጋል።

አጠቃላይ ገንዘብ

የኪንግ ካውንቲ አጠቃላይ ገንዘብ የካውንቲውን መንግስት ልማዳዊ አሰራሮች ይደግፋል፤ ከእነዚህ ውስጥ በርካቶች በግዛት ሕግ መሰረት አስገዳጅ የሆኑ ናቸው።

በጁን 2020፣ አጠቃላይ የገንዘብ ድጋፍ ከ 2021-2022 ጋር የ $150 ሚሊዮን ልዩነት ኖሮት ተበጅቷል።

200917_10279w_KC_GF_revenue_amh

200917_10279w_KC_GF_expend_amh

200917_10279w_KC_balancing_GF_amh

expand_less