Skip to main content

Food safety rating system in Amharic

የምግብ ደሕንነት ምዘና ክፍፍሎች

ስለ ምግብ ቤቶች የምግብ ጥራት ልምምዶች የበለጠ መረጃ ለማሕበረሰቡ ለማቅረብ፤ እንዲሁም ስለ አመጋገብ በመረጃ የተደገፉ ውሳኔዎችን እንዲያደርግ ለመርዳት ምግብ ቤቶች ከአራቱ የምግብ ጥራት ምዘና ደረጃዎች አንዱን ያገኛሉ፡፡

  • መሻሻል ያስፈልገዋል
    ይህ ምግብ ቤት ባለፈው ዓመት ውስጥ በሲያትል እና ኪንግ ካውንቲ – የህብረተሰብ ጤና ተዘግቶ ነበር ወይም ለጤና አደገኛ የሆኑ የምግብ አያያዝ ልማዶችን ለማስተካከል በርካታ ጊዜ በመመላለስ የሚከናወኑ ፍተሻዎች ያስፈልጉት ነበር።
  • ደህና
    ምግብ ቤቱ ባለፉት አራት ፍተሻዎች በርካታ ለጤና አደገኛ የሆኑ የምግብ አያያዝ ልማዶች ነበሩት።
  • ጥሩ
    ምግብ ቤቱ ባለፉት አራት ፍተሻዎች ጥቂት ለጤና አደገኛ የሆኑ የምግብ አያያዝ ልማዶች ነበሩት።
  • በጣም ጥሩ
    ምግብ ቤቱ ባለፉት አራት ፍተሻዎች ምንም ወይም ጥቃቅን የሚባሉ ለጤና አደገኛ የሆኑ የምግብ አያያዝ ልማዶች ነበሩት።

Visual illustration of the four food safety rating emojis in Amharic

ከምግብ ቤቶች ምዘና በስተጀርባ ያለው ምንድን ነው?

የምግብ ቤቶች የምዘና ክፍፍል የሚወሰነው በሁለት ዋና ዋና አካላት ነው:

  • በጊዜያት ውስጥ ያሉ የምግብ ደሕንነት ልምምዶች ሂደት፡፡
    ጥሩ የምግብ ደሕንነት በየዕለቱ መተግበር አለበት፡፡ የምግብ ደሕነት ምዘና የመስኮት ምልክቶች ምግብ ቤቶች በአንድ ነጠላ ምርመራ ብቻ ሳይሆን፤ በረዥም ጊዜያት ውስጥ ምን ያሕል እየተንቀሳቀሱ እንዳለ ያሳያል፡፡ የምግብ ቤቶች የምግብ ጥራት ምዘና የሚወሰነው ምግብ ቤቱ ባለፉት አራት ተከታታይ መደበኛ ቁጥጥሮች ባገኛቸው ደህንነቱ ያልተጠበቀ የምግብ አያያዝ ልምድ አማካኝ ነጥብ ነው፡፡
  • የብቃት ደረጃ፡፡
    የኪንግ ካውንቲ ነዋሪዎች፤ ምግብ ቤቶች ምርመራውን ማለፋቸውን ወይም መውደቃቸውን ባለፈ ማወቅ ይፈልጋሉ፡፡ የምግብ ቤት መስኮት ምልክቶች፤ ምግብ ቤቶች ዝቅተኛውን የመስፈርት ደረጃ ከማሟላት ባለፈ ምን ያህል የምግብ ደሕንነት ልምምዶችን እንደሚለማመዱ ያሳያል፡፡

በ2017 ይህንን ስርዓት ተግባራዊ ባደረግንበት ወቅት በእያንዳንዱ ምድብ ውስጥ የሚገቡ ምግብ ቤቶች መቶኛ በግምት ሲከፋፈል 55% "በጣም ጥሩ" 36% "ጥሩ" እና 8% "መጠነኛ" ነበር። "መሻሻል የሚፈልግ" ምድብ ማለት ምግብ ቤቱ ባለፈው ዓመት በሕብረተሰብ ጤና መምሪያ ተዘግቶ ነበር ወይም ደረጃቸውን ያልጠበቁ የምግብ አያያዝ ልምዶችን ለማስተካከል በርካታ ጊዜ በመመላለስ የሚደረጉ ቁጥጥሮች ያስፈልጉ ነበር ማለት ነው። ይህ ምድብ በአማካይ ነጥብ ላይ የተመሠረተ አይደለም።

Food safety rating percentages in Amharic

ደህንነቱ ያልተጠበቀ የምግብ አያያዝ ልምድ ሲባል ምን ማለት ነው?

እነዚህ የምግብ አያያዝ ልምምዶች፤ እንደሚገባው ካልተተገበሩ፤ በእርግጠኝነት ወደ ምግብ ወለድ በሽታዎች ያመራሉ፡፡

Visual illustration of four key food safety handling in Amharic

expand_less